Skip to main content

ፀሐይ ለቤተሰብ

  • መነሻ ገጽ
  • ኮርሶች
  • ብሎግ
  • ይግቡ
Watch Intro Video

ፀሐይ ለቤተሰብ የወላጅነት ት/ቤት

የልጆችዎን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ የሚረዱ ትምህርቶችን ከባለሞያዎች አሁኑኑ ያግኙ!

ት/ቤታችንን ይቀላቀሉ - ይመዝገቡ

በራስ መተማመንን ለልጆች በማስተማር ልጆችን ትጉህ እና ስኬታማ እንዲሆኑ መርዳት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በራስ የመተማመን ክህሎትን መገንባት

ብዙ ሰዎች በራስ መተማመን በተፈጥሮ የተሰጠ ፀጋ ነው ብለው ያስባሉ፣ ግን አይደለም፡፡ በራስ መተማመን ያለማቋረጥ የሚያድግ ክህሎት ነው። ያለማቋረጥ ስንል ያለማቋረጥ መሞከር፣ ያለማቋረጥ መውደቅ፣ ያለማቋረጥ መነሳት፣ ያለማቋረጥ መማር ማለት ነው። በራስ መተማመን ልዩ የሚያደርገው ሁሉንም ሰው ከሚያመሳስለው ነገር መጀመሩ ነው።

በራስ መተማመን ኮርስ 01 - ይመዝገቡ
Watch Intro Video

ቁጣ ተፈጥሯዊ እና በአግባቡ ከገለጽነው ጤናማ ስሜት ነው። የቁጣ ስሜት ሲሰማን በአግባቡ ማስተናገድ መቻል ትልቅ ክህሎት ሲሆን ልምምድም ይጠይቃል።

ቁጣን በአግባቡ የማስተናገድ ብቃት ማዳበር

ሁሉም ሰው አንዳንዴ ይናደዳል! ቁጣ ለሰው ልጅ ራስን ለመጠበቅ እና ለመከላከል ወሳኝ ውስጣዊ ስሜት ነው፤ ገንቢ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ሲውል ሰዎች እራሳቸውን እና ሌሎችን ለመጠበቅ እና ኢፍትሃዊነትን ለመቋቋም ጥንካሬ እና ድፍረት እንዲያገኙ ይረዳቸዋል።

ቁጣን በአግባቡ ማስተናገድ ኮርስ 02 - ይመዝገቡ
Watch Intro Video

የልጆችን ስሜት ለመለየት እና በነሱ ቦታ ሆነን ነገሮችን ለመረዳት ማህበራዊ እና ስሜታዊ ትምህርትን መማር ወሳኝ እንደሆነ ያውቃሉ?

ማህበራዊና ስሜታዊ ልህቀትን ማስተማር

የሰው ልጅ ስሜታዊ እና ማኅበራዊ እድገት አንዳንድ ጊዜ ከአዕምሯዊ ዕዉቀት የበለጠ አስፈላጊ የሚሆንበት ግዜ አለ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማኅበራዊ እና ስሜታዊ ትምህርትን አንድ ጊዜ ተምረው በዕለት ተዕለት ስራቸው ላይ የሚተገበሩ ተማሪዎች፣ ምንም ዓይነት የማኅበራዊ እና የስሜታዊ ትምህርትን ካልወሰዱ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያሳያሉ።

ማህበራዊና ስሜታዊ ልህቀት ኮርስ 03 - ይመዝገቡ
Watch Intro Video

መልካም የሆነ የወላጅ እና የልጅ ግንኙነትን ጥቅም ማወቅ፣ ከባድ ሁኔታዎችን የሚቋቋሙ እና ደስተኛ ልጆች እንዲኖርዎት እንደሚረዳ ያውቃሉ?

መልካም የሆነ የወላጅ እና የልጅ ግንኙነት መፍጠር

ጤናማ ግንኙነት የሚመሠረተዉ እንዴት ነው? ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረንስ ዕድለኞች መሆን አለብን? በጭራሽ! ግንኙነትን የመገንባት ክህሎት በጊዜ ሂደት የሚማሩት እና ተግባራዊ የሚያደርጉት ነገር ሲሆን፣ ጠንካራ ግንኙነትን መመስረትን ከሁለቱም ወገን ትጋትን እና የማያቋርጥ ጥረት ማድረግን ይፈልጋል።

መልካም የወላጅና የልጅ ግንኙነት ኮርስ 04- ይመዝገቡ
Watch Intro Video

የአዕምሮ ቁስለት ለአንድ ጊዜ የሚፈጠር ሳይሆን በአዕምሯችን ውስጥ የማይታይ ምልክትን ጥሎ የሚያልፍ ክስተት መሆኑን ያውቃሉ?

በፅናት ከስሜት እና ከአዕምሮ ቁስለት የማገገም ጉዞ

በዚህ ትምህርት ውስጥ ተሳታፊዎች በስሜት ቁስል እና በማገገም ሂደት መካከል ያለውን ውስብስብ መስተጋብር በጥልቀት ይረዳሉ። ስለ ፈውስ ሂደት ስነ-ልቦናዊ፣ ስሜታዊ እና አካላዊ ተፅዕኖዎች ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ያገኛሉ። አሳታፊ በሆነ አቀራረብ፣ አቅምን የሚያበረታቱ በማስረጃ የተመሰረቱ ልምምዶችን እና ራስን የመንከባከብ ስልቶችን እንቃኛለን።

በፅናት ከስሜት እና ከአዕምሮ ቁስለት የማገገም ጉዞ ኮርስ 05- ይመዝገቡ
Watch Intro Video

አሉታዊ የአስተሳሰብ ንድፎችን ማወቅ መማር እና በአስተሳሰቦች፣ በስሜቶችዎ እና በባህሪዎችዎ መካከል ያለውን ግንኙነት መረዳት ስጋትን፣ ጭንቀትን እና የእለት ተእለት ተግዳሮቶችን በመቆጣጠር ረገድ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ያውቃሉ?

የግንዛቤ ባህሪ ቴራፒ

በዚህ ኮርስ የግንዛቤ ባህሪ ቴራፒ ፅንሰ-ሀሳብ የምንዳስስ ሲሆን ይህም በየቀኑ የሚደረግ ተግባራዊ ልምምድ እና የማሰላሰያ ጥያቄዎችን በውስጡ የያዘ ነው። አስተሳሰብን እንዲሁም የግንዛቤ መዛባትን በመረዳት ሀሳብ በስሜት እና በባህሪ ላይ የሚያመጣውን ተዕዕኖ በተጨማሪም ውጥረት፥ ጭንቀት እና ድባቴ መንስዔያቸውን እና እንዴት መቆጣጠር ወይም መፍታት እንደምንችል በዝርዝር እናያለን።

የግንዛቤ ባህሪ ቴራፒ ኮርስ 06- ይመዝገቡ
Watch Intro Video

ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ

ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ እ.ኤ.አ በ 2005 የተቋቋመ ሀገር በቀል ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ሲሆን የልጆች፣ የታዳጊዎችን እና የወጣቶችን ህይወት ለማሻሻል ይሰራል። ዊዝ ኪድስ ዘላቂ የሆነ የባህሪ እና ማህበረሰባዊ ለውጦች ለማምጣት እድሜን፣ ቋንቋን፣ ባህልን እና የእድገት ደረጃን ያማከሉ በጥናት የተደገፉ የፈጠራ ስራዎችን ቴሌቪዥን፣ ራዲዮን እና በይነ መረብ/ኢንተርኔት፣ ት/ቤቶችን፣ ፌስቲቫሎች እና ማህበረሰባዊ ስብሰባዎችን ተጠቅሞ በማሰራጨት ከ 10 ሚሊየን በላይ ህፃናትን፣ ታዳጊዎችን እና ቤተሠቦቻቸውን እያገለገለ ይገኛል። ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ ለሀገር እያደረገ ባለው መልካም አስተዋጽኦ በርካታ አለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ ላሉ ህፃናት/ልጆችን እና ወጣቶችን ለመደገፍ ፀሐይ ለቤተሰብ፣ ፀሐይ መማር ትወዳለች፣ የጥበብ ልጆች እና ወጣት ፈጣሪዎች /ተመራማሪዎች የሚሉትን አራት የፈጠራ ስራዎች /ኢኖቬሽኖች ይጠቀማል።

ለበለጠ መረጃ
  • መነሻ ገጽ
  • ሁሉም ኮርሶች
  • ያግኙን
  • የግላዊነት ፖሊሲ
© Copyright Whiz Kids Workshop 2025
Teach online with Thinkific Open in a new window